father
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው፤
መጽሐፈ ምሳሌ 1 : 8
ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፥ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር።
መጽሐፈ ምሳሌ 3 : 11
ጻድቅ ያለ ነውር ይሄዳል፥ ልጆቹም ከእርሱ በኋላ ምስጉኖች ናቸው።
መጽሐፈ ምሳሌ 20 : 7
እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል።
መጽሐፈ ምሳሌ 14 : 26
ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።
መጽሐፈ ምሳሌ 3 : 3
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤
መጽሐፈ ምሳሌ 6 : 20
የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
መጽሐፈ ምሳሌ 23 : 22
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው፤
መጽሐፈ ምሳሌ 1 : 8
በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጻዋል።
መጽሐፈ ምሳሌ 13 : 24
እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
መጽሐፈ ምሳሌ 4 : 1

